Semayawi Support-North America

Home

More on semayawiParty.org site

“ከአገዛዝ ወደ ነፃነት የምንሸጋገርበት ትግል ላይ ነን” ኢ/ር ይልቃል ጌትነት፤ የሰማያዊ ፓርቲ ሊ/መንበር

የሰማያዊና ኦፌኮ ፓርቲ አባላትና አመራሮች መታሰራቸውን ሰማያዊ ፓርቲ ያወገዘ ሲሆን፤ “አሁን የፓርቲ ፖለቲካ የምናደርግበት ጊዜ ላይ አይደለንም፤ ከአገዛዝ ወደ ነፃነት የምንሸጋገርበት ትግል ላይ ነን” ብለዋል የፓርቲው ሊ/መንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት፡፡

[ሙሉውን አስነብበኝ / read more]>

ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ ጥልቅ የሐዘን መግለጫ!

አንድ በስልጣን ላይ የተቀመጠ አካል ተቀዳሚ ተግባር የዜጎችን ደህንነት መጠበቅ መሆኑን ጤነኛ አዕምሮ ያለው የሰው ልጅ የሚገነዘበው ጥሬ ሃቅ ነው፡፡ እንደ እርግማን ዛሬ በኢትዮጵያ የስልጣን እርካቡን የተቆጣጠረው ቡድን የሚገዛቸውን ዜጎች የሚያያቸው እንደጠላት እንጅ የመንግስትን ጥበቃ እንደሚፈልጉ፤ በጠላትነት የፈረጃቸው ዜጎች በከፈሉት ግብር ስልጣን ላይ መቆየት መቻሉን እንኳን ባለስልጣናቱ መረዳት ተስኗቸዋል፡፡

ሰኔ 8 ቀን 2007 ዓ.ም በደብረ ማርቆስ ከተማ እጅግ በሚሰቀጥጥ ጭካኔ እንደ እባብ ተቀጥቅጦ የተገደላው የሰማያዊ ፓርቲ ቆራጥ ታጋ ይ ሳሙኤል አወቀ የስርዓቱ አገልጋዩች ለዓመታት ሲያስፈራሩት፣ ሲደበድቡት፣ ሰርቶ የመኖር መብቱን ሲጋፉት፣ ያልተሳከ የመግደል ሙከራ በተደጋጋሚ ጊዜ ሲፈፅሙበት መቆየታቸውን የሚያረጋግጡ በርካታ ማስረጃዎች ተይዘዋል፡፡ ሳሙኤል ሕይወቱ አደጋ ላይ እንደሆነችና ጥበቃ እንዲያደርጉለት የጠየቃቸው የፀጥታና የፍትህ አካላት በተገላቢጦሽ ተጨማሪ ዛቻና ማስፈራሪያ ያደርሱበት እንደነበር አይዘነጋም፡፡ አንድ ወጣት በተወለደበት ምድር በሕይወት የቆየባቸውን ጊዚያት በስጋት እንዲኖር ከተፈፀመበት ግፍ በተጨማሪ በሕይወት የመኖር መብቱ በአረመኔዎች እጅ ስትነጠቅ የህዝብን ፀጥታና ደሕንነት እናስከብራለን የሚሉ አካላት በመሃል ከተማ እንኳን ደርሰው ለመታደግ አቅሙም ሆነ ፍላጎቱ አልነበራቸውም፡፡

[ሙሉውን አስነብበኝ / read more]>

የሳሙኤል አወቀ መገደል የነፃነት ትግሉን አያስቆመውም !!

“ለማንኛውም የምከፍለው ዋጋ ለለሃገሬና ለነፃነት ነው፡፡ በአካል ብታሰርም ህሊናዬ አይታሰርም፡፡ ከገደሉኝም ትግሌን አደራ!!! አገራችን የወያኔ ዘረኞች ብቻ መፈንጫ መሆን የለባትም! ትግላችን የነፃነት፤ ጉዞአችን ጎርባጣ፤ መድረሻችን ነፃነት፤ ታሪካችን ዘላለማዊ ነው፡፡” ሳሙኤል አወቀ ፊስቡክ ገፅ ላይ የተገኘ ሰኔ 8/2ዐዐ7 ዓ.ም፡፡

ምስራቅ ጎጃም ግንደ ወይን 1978 ዓ/ም ተወልዶ – በህግ የዲፕሎማ እና ዲግሪውን ሰርቷል፡፡ ሣሙኤል አወቀ የሠማያዊ ፓርቲ መስራች አባልና ከዚያም በፊት እንደ ሌሎች ጓደኞቹ ከቅንጅት ጀምሮ በአንድነት ፓርቲ ውስጥ ሲታገል የቆየ ጠንካራ ኢትዮጵያዊ ነበር፡፡ ሣሙኤል በሙያው የህግ ባለሙያና በጥብቅና ስራ በግል እየሠራ ጎን ለጎን ደግሞ ለአገሩ ከነበረው ፅኑ ፍቅር የተነሣ በሠላማዊ ትግል በማመን ገና በልጅነቱ ትግሉን ተቀላቅሎ በግፍ እስከተገደለ ድረሥ በንቁ የፖለቲካ አመራር ሲታገል ቆይቷል፡፡ ሣሙኤል የሠማያዊ ፓርቲ ከተመሠረተ ጀምሮ በከፍተኛ ኃላፊነት በንቃትና በተደራጀ መልኩ በተወከለበት ቀጠና በምስራቅ ጎጃም ዞን ሲያደራጅና ሲያስተባብር ነበር፡፡

[ሙሉውን አስነብበኝ / read more]>

Semayawi Party Chairman Yilkal Getnet on Current Ethiopian Affairs

የአንድነት ሰሜን አሜሪካ ድጋፍ ማህበርና የሰማያዊ ሰሜን አሜሪካ ድጋፍ ማህበር የተሰጠ የጋራ መግለጫ

በሰሜን አሜሪካ የሰማያዊ እና የአንድነት ፓርቲዎች ድጋፍ አሰባሳቢ ድርጅቶች በትብብር ለመስራት መስማማታቸው ይታወሳል። በስምምነቱ መሰረት የመጀመሪያው የጋራ ስራቸውን የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበርን የሰሜን አሜሪካ የስራ ጉብኝት በጋራ ማስተባበር አድርገው ጀምረዋል፡፡ በዚህም መሰረት የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ ይልቃል ጌትነት በጋራ ኮሚቴው በተደረገላቸው ጥሪ መሰረት በመጪው ሚያዚያ (ኤፕሪል) ውስጥ በሰሜን አሜሪካ የስራ ጉብኝት ለማድረግ ዝግጅታቸውን አጠናቀዋል፡፡ የጉብኝቱ ዋና ዓላማ፤ በመጪው ግንቦት በሚካሄደው ምርጫ ውስጥ ለሚሳተፉ የሰማያዊ ፓርቲ እጩዎች ገንዘብ ማሰባሰብ ሲሆን፤ በተጨማሪም፤ በኢትዮጵያ የምርጫ ሂደት ምን ይመስላል፣ ምርጫው ውስጥ መቆየት ያለው ፋይዳ፣ የሰማያዊ ፓርቲ አጠቃላይ ገፅታና እንቅስቃሴ ምን ይመስላል፣ በሚሉት ጥያቄዎች ላይ ውይይት ይደረጋል፡፡ የፓርቲውን የሰላማዊ ትግል ስትራቴጂዎች በውጭ ሀገር ለሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ማስረዳትና በነዚህ ጉዳዮች እንዲሁም ባጠቃላይ የአገራችን ወቅታዊ ሁኔታዎች ዙሪያ ከኢትዮጵያዊያን ጋር ዉይይት ማኪያሄድም የዝግጅቱ አካል ነው፡፡ የጉብኝቱ ጊዜያዊ መርሃ ግብር እንደሚከተለው ሲሆን ወደፊት እነደየሁኔታው ሊቀየር፤ ሊጨመር፤ ወይም ሊቀነስ የሚችል መሆኑንም አስቀድመን እናሳስባለን። የየከተሞቹ ዝርዝር ፕሮግራም በቅርቡ በመገናኛ ብዙኋን ይፋ የሚደረግ ሲሆን፤ በተለያዩ ከተሞች የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ባቅራቢያቸው በሚደረጉት የዉይይት መድረኮች ላይ ተሳታፊ በመሆን ስለኢትዮጵያ አገራችን እንዲሁም ስለወገናችን የወደፊት እጣፈንታ ዉይይት እንዲያካሂዱ ኮሚቴዉ ጥሪዉን ያስተላልፋል። በየከተሞች የምትገኙ የሰማያዊ እና የአንድነት ድጋፍ ሰጪ ማህበራት አባላትም ይህ ፕሮግራም የተሳካ እንዲሆን የበኩላችሁን አስተዋጽኦ እንድትለግሱ የጋራ ኮሚቴዉ ጥሪ ያደርጋል። ከአክብሮት ሰላምታ ጋር የሰማያዊ እና የአንድነት የሰሜን አሜሪካ የድጋፍ ድርጅቶች የጋራ ኮሚቴ ለበለጠ መረጃ info@semayawiusa.org ኢሜል በማድረግ ወይም በ (202) 556 – 3078 መልክት በመተው አዘጋጅ ኮሚቴዉን ሊያገኙ ይችላሉ።

የአንድነት ሰዎች ሰማያዊን እየተቀላቀሉ ነው

የአንድነት ለፍትሕና ለዲሞክራሲ አባላት የነበሩ አሁን የሰማያዊ ፓርቲን ለመቀላቀል ሠነዶችን እየፈረሙ መሆናቸው ተገልጿል፡፡ አንዳንድ የአመራር አባላትን የጨመረው ይህ እርምጃቸው “ለጀመሩት ሕጋዊና ሰላማዊ ትግል ተገቢ አማራጭ ነው” ብለዋል። የሰማያዊ ፓርቲ መሪዎችም ሕጉ በሚፈቅደው መሠረት የአባልነት ማመልከቻቸውን መቀበላቸውን ይናገራሉ።

[ሙሉውን አስነብበኝ / read more]>

ሰበር ዜና – የአንድነት አባላት በይፋ ሰማያዊ ፓርቲን ተቀላቀሉ

(ሰማያዊ ፓርቲ) ብሄራዊ ምርጫ ቦርድና ኢህአዴግ በወሰኑብን ፖለቲካዊ ውሳኔ ምክንያት አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲን ተነጥቀናል ያሉ የአንድነት ፓርቲ አባላት› በይፋ ሰማያዊ ፓርቲን መቀላቀላቸውን አስታወቁ፡፡ በእነ በላይ ፍቃዱ አመራርነት አንድነት ፓርቲን በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ሲመሩ የነበሩ አመራሮች ዛሬ ጥር 26 ቀን 2007 ዓ.ም በሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቁት ከቀድሞ ፓርቲያቸው አንድነት ጋር የፕሮግራምም ሆነ የስትራቴጂ ተመሳሳይነት ወዳለው ሰማያዊ ፓርቲ ተቀላቅለው ሰላማዊ ትግላቸውን ለመቀጠል መወሰናቸውን ይፋ አድርገዋል፡፡ መግለጫውን የ‹ቀድሞው አንድነት ፓርቲ› አፈ ጉባዔ የነበሩት አቶ አበበ አካሉ፣ ምክትል አፈ ጉባዔው አቶ ፀጋዬ አላምረው፣ የአዲስ አበባ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ነገሰ ተፋረደኝ እንዲሁም የወጣቶች ጉዳይ ኃላፊው አቶ ስንታየሁ ቸኮል ሌሎችን በመወከል ሰጥተዋል፡፡ ‹‹የምናምነው በሰላማዊ ትግል ብቻ ነው፡፡ ይህን ሰላማዊ ትግል ለመምራት ደግሞ ሰማያዊ ፓርቲ ብቁ ነው ብለን በማመን ፓርቲውን ተቀላቅለናል›› ብለዋል በመግለጫው ላይ የተወከሉት አዲሶቹ የሰማያዊ አባላት፡፡ በዚህ መሰረትም በርከት ያሉ አመራሮችና አባላት በይፋ የሰማያዊ ፓርቲ የአባልነት ፎርም ሞልተዋል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ የአንድነት አባላት ሰማያዊ ፓርቲን መቀላቀላቸውን አስመልክቶ መግለጫ ለመስጠት ወደ ሰማያዊ ቢሮ ባቀኑበት ወቅት ፖሊስ ሰማያዊ ፓርቲ ቢሮ ድረስ በመግባት ‹‹በሰማያዊ ስም መግለጫ የሚሰጡ አካላት እንዳሉ ሰለሰማን ነው›› በሚል ለፓርቲው አመራሮች ጥያቄዎችን አቅርበዋል፡፡

‹‹ህገ መንግስቱን በመናድ›› የተከሰሱት እስረኞች ከተቀጠረባቸው ቀን ቀድመው ተፈቱ::

ሰሱት እስረኞች ከተቀጠረባቸው ቀን ቀድመው ተፈቱ

በሰላማዊ ሰልፉ ወቅት ታፍሰውና ደብደባ ተፈጽሞባቸው ከታሰሩ በኋላ ፍርድ ቤት ቀርበው ‹‹ህገ መንግስቱን በመናድ፣ መስቀል አደባባይ ላይ ንብረት በማውደም፣ በሁከትና ብጥብጥ›› እና በመሳሰሉት ክሶች ተከሰው እስከ 14 ቀን ቀነ ቀጠሮ ተሰጥቶባቸው የነበሩት የሰማያዊና የሌሎች የ9ኙ ፓርቲዎች አመራሮች፣ አባላትና የሰልፉ ተሳታፊዎች በመታወቂያ ዋስ እንዲፈቱ ተወሰነ፡፡

[ሙሉውን አስነብበኝ / read more]>

Fifty Two Detainees Start Hunger Strike

Fifty two detainees held at Addis Ababa Police Station (3rd-Station) have started a hunger strike to protest solitary confinement of 9 of their colleagues, who are held in a dark and freezing cells for 24 hours a day, and a ban family visitation. Detainees have started refusing food starting Wednesday , December 10, 2014 and planned to last for t until their demands are met. They have inquired the prison administration to let members of their family and friends visit them; most importantly they have demanded that those who are kept separately in a dark and freezing cells to join other detainees ( 9 detainees, including Party Chairperson, Eng. Yilkal Getnet, are held in a cold and dark cell for the entire 24 hours behind closed doors). The detainees are demanding the prison administration to respect their basic human rights while they are in custody. Members of their families and The Party are deeply worried about the condition in which detainees are being held. Many of the detainees are in need of medical attention due to savage beating that took place on Saturday December 6, 2014. Contact: Yonthan Tesfaye , Head of Public Relations, Semayawi (Blue) Party

የሰማያዊ ፓርቲ ብሄራዊ ምክር ቤት ውሳኔዎችን አስተላለፈ

‹‹አገዛዙ የወሰደውና ወደፊት የሚወስደው ከእስካሁኑ የባሰ አረመኔነት እርምጃ ይበልጡን ያጠናክረናል›› የሰማያዊ ፓርቲ ብሄራዊ ምክር ቤት ትናንት ህዳር 30/2007 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ ትግሉን ያጠናክራሉ ያላቸውን ውሳኔዎችን አስተላለፈ፡፡ ብሄራዊ ምክር ቤቱ ያስተላለፋቸው ውሳኔዎች ‹‹ህወሓት/ኢህአዴግ በፈፀመው ጭካኔ የተሞላበት እርምጃ እና እስር ምክንያት ክፍተት ሳይፈጠር የፓርቲው እንቅስቃሴ እንዲቀጥልና ትግሉም እንዲጠናከር የሚያስችሉ ናቸው›› ሲሉ የብሄራዊ ምክር ቤቱ ሰብሳቢ አቶ ሰይድ ኢብራሊም ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ብሄራዊ ምክር ቤቱ ባወጣው መግለጫ ህወሓት/ኢህአዴግ በአመራሩ፣ አባላቱና ደጋፊዎቹ ላይ የፈጸመው ጭካኔ ለሰላማዊ ታጋዮች ባለው ጥልቅ ጥላቻና ጭካኔ በተሞላበት እርምጃው ከትግሉ ያፈገፍጋሉ ከሚል ስሌት እንደሆነ በመግለጽ ‹‹አገዛዙ የወሰደውና ወደፊትም ሊወስደው የሚችለው ከእስካሁኑ የባሰም አረመኔነት የተሞላበት እርምጃ ይበልጡን ያጠናክረናል እንጅ ከትግላችን ቅንጣት ያህል ወደኋላ እንደማናፈገፍግ›› ብሏል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በአንድ በኩል ‹‹ምንም ችግር ሳይፈጥሩ በቁጥጥር አዋልናቸው›› ያላቸውን ሰላማዊ ታጋዮች በሌላ በኩል ፍርድ ቤት አቅርቦ ‹‹መስቀል አደባባይ ላይ ንብረት አውደመዋል›› ሲል መክሰሱም በገዥው ፓርቲ የሚዘወሩ ተቋማት በጉዳዪ ላይ አንድ አይነት አቋም እንደሌላቸውና ይህም የተጀመረው ሰላማዊ ትግል ስርዓቱን መያዣ መጨበጫ እንዳሳጣው ያሳያል ብሏል፡፡ ከህወሓት/ኢህአዴግ ከዚህ የባሰ ጭካኔን እንጠብቃለን ያለው ምክር ቤቱ ‹‹በምናደርገው ትግል ሁሉ የሚጠበቅብንን መስዋእትነት ለመክፈልና ሀገራዊ ግዴታችንን ለመወጣት ዝግጁ መሆናችን እየገለጽን መስዋዕትነት ለመክፈል የተዘጋጀንለትና የምናከብረው ህዝብ ከጎናችን እንዲቆም›› ሲል ጥሪውን አስተላልፏል፡፡ ምክር ቤቱ እሁድ ታህሳስ 5/2007 ዓ.ም መደበኛ ስብሰባ የጠራ ሲሆን የተላለፉት ውሳኔዎች በምን መልኩ ተግባራዊ እንደሚሆኑ ተወያይቶ ውሳኔ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ኢ/ር ይልቃል ጌትነት፣ ብርሃኑ ተክለያሬድ፣ ጋዜጠኛ በላይ ማናዬና ሌሎቹም ለየብቻቸው ጨለማ ቤት ታስረዋል

ኢ/ር ይልቃልን ከመኪና ገፍትረው ሊጥሏቸው ነበር ህዳር 27/2007 ዓ.ም ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ታፍሰው ከታሰሩት መካከል አብዛኛዎቹ ጨለማ ቤት መታሰራቸው ታወቀ፡፡ ከሰማያዊ ጽ/ቤት አካባቢ በጀመረው ሰልፍ ላይ ታፍሰው አዲስ አበባ ፖሊስ ጣቢያ (ሶስተኛ) ታስረው የሚገኙት መካከል ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት፣ ብርሃኑ ተክለያሬድ፣ ጋዜጠኛ በላይ ማናዬና ሌሎቹም ለየ ብቻቸው ጨለማ ቤት መታሰራቸው ታውቋል፡፡ ታሳሪዎቹ ትናንት ህዳር 27/2997 ዓ.ም ምሽት ላይ ከጨርቆስ ፖፖላሬ እስር ቤት ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ጣቢያ (ሶስተኛ) የተዛወሩ ሲሆን ‹‹ምርመራ ላይ ናቸው፡፡›› በሚል እንዳይጠየቁ ተደርገዋል፡፡ በሌላ በኩል ከሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት አካባቢ የተነሳው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ተሳታፊ ከነበሩት መካከል አብዛኛዎቹ እግርና እጃቸውን እንደተሰበሩ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ከዚህም ባሻገር የታፈሱት አመራሮች በፒክ አፕ መኪና ተጭነው በሚወሰዱበት ወቅት ደህንነቶች ኢንጅነር ይልቃል ጌትነትን ከመኪናው ላይ ገፍተው ለመጣር ሙከራ አድርገው እንደነበርና አብረው የተጫኑት ታሳሪዎች ይዘው እንዳስቀሯቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡

Hundreds detained, many suffer broken arms and legs

ADDIS ABABA (Dec 7) - Senior opposition party leaders and three busloads of protesters were admitted to the 3rd Police Station on Saturday night, eye-witnesses said. The 3rd police station is adjacent to the infamous Maekelawi Prison in the capital. Many of the arrested were limping with injuries from police beatings. Engineer Yilikal Getnet, chairman of Semayawi Party, reportedly suffered a broken hand.Families and friends who tried to take food and clothing to the detainees at the 3rd Police Station and elsewhere, were turned back, without passing the essentials. Other activists who suffered beatings were also being held at Kazanchis and Cherkos police stations.

Ethiopia: Senior Blue Party leaders, members and supports have been detained December 6, 2014

On Saturday, December 6,2014, the ethnic based Ethiopian government security forces have arrested leaders of Blue and other Party leaders,Senior Blue Party leaders, members and supports have been detained members and supporters at the start of a peaceful public rally to demand free and fair election. Blue Party Chairman Eng. Yilkal Getnet along with senior party members have been detained. This protest rally was organized by a coalition of opposition political parties fully in compliance with the law. This is a clear manifestation of the governing party’s total dictatorship and absolute intolerance for peaceful decent At this point, the exact number of detainees is not available nor where they have been detained. We will release more information soon.

[ሙሉውን አስነብበኝ / read more]>

Semayawi Party office in Ethiopia's capital surrounded by police and kidnapped more members

Federal Police surrounded Semayawi Party's office in Addis Ababa, Ethiopia, ahead of the 24 hour protest demonstration that was called by a coalition of 9 opposition groups for this coming weekend. The protest is planned to be held at Meskel Square. 10 semayawi and AEUP members are kidnapped by the Ethiopian Junta/Gov`t Security forces

[ሙሉውን አስነብበኝ / read more]

Eng. Yilkal Getnet’s Powerful Message “We’ll Do It”